እንኳን ደስ አለን! እንኳን ደስ አላችሁ!
የላፍቶ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በተማሪዎች የወንዶች የእግር ኳስ ዉድድር ዋንጫ የበላን ሲሆን በቀጣይም ክፍለ ከተማዉን ወክለዉ ለከተማ የሚወዳደሩ ይሆናል!! በድጋሚ እንኳን ደስ አለን!
በመምህራን እና በተማሪዎች ሁለት ዋንጫ ወስደናል: እንስራ ዉጤት በጊዜዉ ይመጣል!!
ላፍቶ ወደፊት......... የሴት ተማሪዎች እግርኳስ ቡድን ለዋንጫ ፍልሚያ ደርሰዉ እጅግ ሳቢ ጨዋታ ቢጫወቱም ነጥብ ይዞ መዉጣት አልተቻለም: በዚሁ መሰረት የሁለተኝነት ደረጃን ይዘዉ አጠናቀዋል: በድጋሚ ለተማሪዎቻችን ያለንን ልባዊ ክብር ለመግለፅ እንወዳለን።